በተለያዩ የህንድ ስቴቶች ማለትም በኬራላ፣ ካርናታካ፣ ዌስት ቤንጋል እና ፓንጃብ ስቴቶች እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 22 እስከ ዲሴምበር 4 ቀን 2023 የአገራችንን ባህል፣ ሙዚቃና አለባበስን ሲያስተዋውቅ ለነበረው ለሙሉአለም የባህል ቡድን አባላት እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 3 ቀን 2023 የምስጋና ፕሮግራም በሚሲዮኑ ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ ላይ የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ የባህል ቡድኑ በደቡብ፣ በምስራቅ እና በሰሜን የህንድ ክፍል በሚገኙት በአራት ስቴቶች ላቀረበው የተለያዩ ባህላዊ ትርኢቶች ከፍ ያለ ምስጋና በማቅረብ የባህል ቡድኑ ህብረብሔራዊት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን በማስተዋወቅ የአገራችንን ገፅታ በአዎንታዊነት ለመገንባት ባደረገው የማስተዋወቅ ሥራ እጅግ በጣም ኮርተንባችኋል ብለዋል። አያይዘውም ለባህል ቡድኑ ፕሮግራሙ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላደረጉት ለህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ICCR)፣ ለአማራ ክልላዊ መንግስትና ለሌሎች የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
በመቀጠል በፕሮግራሙ የተገኙት GTTC India-Ethiopia Forum Dr. Renne Joy እና የGTTCI India ፕሬዚዳንት Dr. Gaurav Gupta የባህል ቡድኑ በአራቱም የህንድ ግዛቶች የአገራችንን ባህል ለማስተዋወቅ ላደረገው ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ ከባህል ቡድኑ ጋር የሁለቱን አገሮች ባህል ለማስተዋወቅ በጋራ እንደሚሰሩ ቃል በመግባት ለቡድኑ አባላት የህንድ ባህላዊ ስጦታ አበርክተዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook