በታይላንድ ታስረው የነበሩ 38 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ተደረገ
_____________________________
በስራ ቅጥር ሽፋን በህገወጥ አለምአቀፍ የሰው አዘዋዋሪዎች ወደ ማይናማር ተወስደው ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች ቀጥለዋል።
ከሰሞኑ በህንድ ኒውዴልሂ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሲዮን የልዑካን ቡድን ወደ ታይላንድ በመላክ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንዲለቀቁ አድርጓል።
ማይናማር ውስጥ ከነበሩት ከስቸጋሪ ሁኔታ አምልጠው ወደ ታይላንድ የሚገቡ ስደኞች ህጋዊ ዶክመንት ባለመያዛቸው ለእስር ታደርገው ነበር።
በኒውዴልሂ የኢትዮጵያ ሚስዮን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ባደረገው ጥረት 38 ኢትዮጵያዊን ከእስር ተለቀው ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉ ታውቋል።
ኢትዮጵያውያንን በህክምና እና በኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራ ታገኛላችሁ በሚል የተሳሳተ መረጃ ወደ ታይላንድ ከዛም ወደ ማይናማር እየተወሰዱ ህገወጥ ስራዎችን እንዲፈፅሙ የሚደረጉ ሲሆን ለከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተዳረጉ ይገኛል።
ችግሩን ለመቅረፍ መንግስት ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።