የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ (የልደት፣ጋብቻ፣ፍቺ፣ ሞት እና ጉዲፈቻ) የምስክር ወረቀት
- በልደት ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
- ሚሲዮኑ ባለበት የተከሰተ ልደትን ለማስመዝገብ የህፃኑ መላጆች ወይም ከወላጆች አንዱ ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት፣
- ልደት የሚመዘገበው በህይወት ለተወለደ ወይም በህይወት ተወልዶ ወዲያውኑ ለሞተ ሲሆን ሞቶ የተወለደ ከሆነ ግን አይመዘገብም፣
- አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ስደተኝነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፣
- በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፣
- የልደት አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፣
- የህፃኑ አሳዳሪ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ህጋዊ የሳዳሪነት ወይም ተንከባካቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- እድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ስደተኛ ወላጆቹን የሚገልጽ ማስረጃ ከስደተኞች መረጃ ዳታ ቤዝ ወይም ዳታ ቤዝ ላይ መረጃው የሌለ እንደሆነ ስደተኛውን በመጠየቅ መመዝገብ አለበት፣
- ከወላጆቹ አንዱ የውጪ አገር ዜጋ ከሆነ የህፃኑ ዜግነት በኢትዮጵያዊ ወላጁ ውሳኔ መሠረት ይመዘገባል፣
- በየጋብቻ አፈፃፀም ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
- ወንድም ሆነ ሴት 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈፀም አይችሉም፣
- በቀጥታ የስጋ ዘመዳሞች ወይም በወላጆችና በተወላጆች መካከል ጋብቻ መፈፀም ክልክል ነው፣
- በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈፀም ክልክል ነው ፣
- ማንኛውም ተጋቢ አስቀድሞ በጋብቻ ከተሳሰረ ከሆነ ይሄው ጋብቻ ፀንቶ በቆየበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ አይመዘገብም፣
- ጋብቻ ሲፈፀም ሁለቱም ተጋቢዎች በአካል ቀርበው ክብር መዝገቡ ላይ መፈረም አለባቸው፣
- በሙሽራው በኩለ ሁለት በሙሽሪት በኩል ሁለት በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፣
ደጋፊ ማስረጃዎች
- ተጋቢዎች ማንበታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት መታወቂያ ወይም የስደተኛ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነተን ሊገልጽ የሚችል ማስረጃ ማቅረብ፣
- ተጋቢዎች ከዚህ በፊት አግብተው የተፋቱ ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለ ማቅረብ አለባቸው፣
- ከ6 ወር ወዲህ በተአሳሳጥ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሦስት በአራት የሆነ የተጋቢዎች ፎቶ ግራፍ መቅረብ አለበት፣
- በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች መስክሮች ወይም በጋብቻ ስርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገቡ ሹም ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፣
- የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፣
- ለፍቺ ምዝገባ መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
- ፍቺው ስልጣን ባለው ፍርድቤት የተፈፀመ መሆን አለበት፣
- የፍቺ አስመዝጋቢ ሆነው የሚቀርቡት ተፋቺዎች በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ ወይም የተፋቺዎች ልዩ ውክልና ያለው መሆን አለበት፣
- የፍ/ቤት የውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፣
- የተፋቺዎች ጊዜው ያላለፈበት የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፖስፖርት ወይም ማህበራዊ መታወቂያ ወይም ስደተኝነትን የሚገልፅ ማስረጃ መቅረብ አለበት፣
- ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት ወስደው እንደሆነ መመለስ አለበት፣
- ለሞት ምዝገባ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
- ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፣
- የሟችን ማንነት የሚገልጽ ማስረጃ የመኖሪያ ፈቀድ ወይም ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነተን ሊገልጽ የሚችል ማስረጃ ማቅረብ አለበት፣
- ውጭ ሀገር ለሞተ አስመዝጋቢ ከሀገሩ መንግስት የሞት ምስክር ወረቀት የዞ መቅረብ አለበት፣
- ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰቡ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፣
- ሟች የመከላከያ ሠራዊት ከሆነ የሟች የጉዳት ሁኔታ መግለጫ ቅጽ መቅረብ አለበት፣
- በጉዲፈቻ ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች
- ጉዲፈቻ የተደረገው ልጅ የቀድሞ የልደት ምስክር ወረቀት ካለው ለምዝገባው ሂደት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ከምስክር ወረቀቱ ከተወሰዱ በኋላ ለክብር መዝገብ ሹም መመለስ አለበት፣
- አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት መታወቁያ መኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ማህበራዊ መታወቂያ ማቅረብ አለበት፣
- በፍርድ ቤት የፀደቀ የጉዲፈቻ ስምምነት ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፣
- የጉዲፈቻ አድራጊዎች የጋብቻ ሁኔታ የሚገልጽ ማስረጃ መቅረብ አለበት፣
የወሳኝ ኩነት ምስክር ወረቀት ክፍያ የአገልግሎት ዋጋ
ተ.ቁ |
በውጭ ሀገር በ USD |
||||||
የኩነቱ ዓይነት |
በመደበኛ ጊዜ |
የዘገየ |
ጊዜው ያለፈበት |
እርማት |
ቅጂ |
ማረጋገጫ |
|
1 | ልደት | 30 | 40 | 50 | 40 | 50 | 20 |
2 | ጋብቻ | 30 | 40 | 50 | 40 | 50 | 20 |
3 | ፍቺ | 30 | 40 | 50 | 40 | 50 | 20 |
4 | ሞት | 20 | 30 | 40 | 30 | 50 | 20 |
5 | ጉዲፈቻ | 30 | 40 | 50 | 40 | 50 | 20 |
ማሳሰቢያ፡-
- መደበኛ የምዝገባ ጊዜ ልደት በ90 ቀን ሲሆን የተቀረው ኩነት በሙሉ በ30 ቀን ውስጥ መመዝገብ አለበት
- በመደበኛው የምዝገባ ወቅት ሳይመዘገብ ቀርቶ እስከ አንድ ዓመት ባለው የዘገየ ሲሆን
- ከአንድ ዓመት በኋላ የሚደረግ ምዝገባ ጊዜው ያለፈበት ይሆናል፡፡