18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ‘’ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት’’ በሚል መሪ ሀሳብ በኒው ዴልሂ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በድምቀት ተከብሯል ።
የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክብርት አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት በበዓሉ አከባበር ላይ ንግግር እና የፓናል ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በውይይቱም ስለ ፌዴራሊዝም እና ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራል ስርዓት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና የሰላም ግንባታ እና ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ሰፊ ገለፃ አድርገዋል። ክብርት ምክትል የሚሲዮኑ መሪ፣ ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋዎች፣ ባህልሎችና እሴቶች ባለቤት እና መፍለቂያ መሆኗን በመጥቀስ፣ ህብረብሔራዊ አንድነታችን ላይ አተኩረን በመስራት የአገራችንን የላቀ ሰላም፣ ዕድገት እና ብልፅግና ለማረጋገጥ ተባብረን መስራት አለብን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።