የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ነፃ የንግድ ቀጣና የብሪክስ አባል ሃገራት ያላቸውን አቅም አሟጥጦ ለመጠቀም በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ከግሎባል ኢንዲያ ቢዝነስ ፎረም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና በአግሮ ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው የባለሃብቶች ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ከህንድ ፤ከሩሲያ፤ከቻይና እና ከብራዚል ባለሃብቶች፤ኤምባሲዎችና የኢንቨስትመንት ተቋማት ጋር አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በፓርኮቹ ለመሳብ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈጻሚው በውይይቱ ገልጸዋል።
በተለይም የብሪክስ አባል ሃገራት ያላቸውን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም አሟጥጦ ለመጠቀም የሚያስችል ስራዎች በመስራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የግሎባል ኢንዲያ ቢዝነስ ፎረም ፕሬዚዳንት ዶክተር ጅቴንድራ ጆሺ፤ የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም በፋርማሲዩቲካል እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችል ቅድመ ኢንቨስትመንት መረጃ ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ የቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን የስራ እንቅስቃሴንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ከ12 በላይ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ያላቸው ህንዳውያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በፋርማሲዩቲካል፣ በቴክስታይል እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፎችበመሰማራት ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ፈጥረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook