Vital Events

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ (የልደት፣ጋብቻ፣ፍቺ፣ ሞት እና ጉዲፈቻ) የምስክር ወረቀት

  1. በልደት ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
    • ሚሲዮኑ ባለበት የተከሰተ ልደትን ለማስመዝገብ የህፃኑ መላጆች ወይም ከወላጆች አንዱ ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት፣
    • ልደት የሚመዘገበው በህይወት ለተወለደ ወይም በህይወት ተወልዶ ወዲያውኑ ለሞተ ሲሆን ሞቶ የተወለደ ከሆነ ግን አይመዘገብም፣
    • አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ስደተኝነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፣
    • በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፣
    • የልደት አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፣
    • የህፃኑ አሳዳሪ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ህጋዊ የሳዳሪነት ወይም ተንከባካቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
    • እድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ስደተኛ ወላጆቹን የሚገልጽ ማስረጃ ከስደተኞች መረጃ ዳታ ቤዝ ወይም ዳታ ቤዝ ላይ መረጃው የሌለ እንደሆነ ስደተኛውን በመጠየቅ መመዝገብ አለበት፣
    • ከወላጆቹ አንዱ የውጪ አገር ዜጋ ከሆነ የህፃኑ ዜግነት በኢትዮጵያዊ ወላጁ ውሳኔ መሠረት ይመዘገባል፣
  1. በየጋብቻ አፈፃፀም ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
    • ወንድም ሆነ ሴት 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈፀም አይችሉም፣
    • በቀጥታ የስጋ ዘመዳሞች ወይም በወላጆችና በተወላጆች መካከል ጋብቻ መፈፀም ክልክል ነው፣
    • በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈፀም ክልክል ነው ፣
    • ማንኛውም ተጋቢ አስቀድሞ በጋብቻ ከተሳሰረ ከሆነ ይሄው ጋብቻ ፀንቶ በቆየበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ አይመዘገብም፣
    • ጋብቻ ሲፈፀም ሁለቱም ተጋቢዎች በአካል ቀርበው ክብር መዝገቡ ላይ መፈረም አለባቸው፣
    • በሙሽራው በኩለ ሁለት በሙሽሪት በኩል ሁለት በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፣

ደጋፊ ማስረጃዎች

  • ተጋቢዎች ማንበታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
  • የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት መታወቂያ ወይም የስደተኛ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነተን ሊገልጽ የሚችል ማስረጃ ማቅረብ፣
  • ተጋቢዎች ከዚህ በፊት አግብተው የተፋቱ ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለ ማቅረብ አለባቸው፣
  • ከ6 ወር ወዲህ በተአሳሳጥ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሦስት በአራት የሆነ የተጋቢዎች ፎቶ ግራፍ መቅረብ አለበት፣
  • በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች መስክሮች ወይም በጋብቻ ስርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገቡ ሹም ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፣
  • የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፣
  1. ለፍቺ ምዝገባ መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
    • ፍቺው ስልጣን ባለው ፍርድቤት የተፈፀመ መሆን አለበት፣
    • የፍቺ አስመዝጋቢ ሆነው የሚቀርቡት ተፋቺዎች በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ ወይም የተፋቺዎች ልዩ ውክልና ያለው መሆን አለበት፣
    • የፍ/ቤት የውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፣
    • የተፋቺዎች ጊዜው ያላለፈበት የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፖስፖርት ወይም ማህበራዊ መታወቂያ ወይም ስደተኝነትን የሚገልፅ ማስረጃ መቅረብ አለበት፣
    • ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት ወስደው እንደሆነ መመለስ አለበት፣
  1. ለሞት ምዝገባ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
    • ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፣
    • የሟችን ማንነት የሚገልጽ ማስረጃ የመኖሪያ ፈቀድ ወይም ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነተን ሊገልጽ የሚችል ማስረጃ ማቅረብ አለበት፣
    • ውጭ ሀገር ለሞተ አስመዝጋቢ ከሀገሩ መንግስት የሞት ምስክር ወረቀት የዞ መቅረብ አለበት፣
    • ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰቡ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፣
    • ሟች የመከላከያ ሠራዊት ከሆነ የሟች የጉዳት ሁኔታ መግለጫ ቅጽ መቅረብ አለበት፣
  1.  በጉዲፈቻ ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች
    • ጉዲፈቻ የተደረገው ልጅ የቀድሞ የልደት ምስክር ወረቀት ካለው ለምዝገባው ሂደት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ከምስክር ወረቀቱ ከተወሰዱ በኋላ ለክብር መዝገብ ሹም መመለስ አለበት፣
    • አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት መታወቁያ መኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ማህበራዊ መታወቂያ ማቅረብ አለበት፣
    • በፍርድ ቤት የፀደቀ የጉዲፈቻ ስምምነት ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፣
    • የጉዲፈቻ አድራጊዎች የጋብቻ ሁኔታ የሚገልጽ ማስረጃ መቅረብ አለበት፣

 

የወሳኝ ኩነት ምስክር ወረቀት ክፍያ የአገልግሎት ዋጋ

 

ተ.ቁ

በውጭ ሀገር በ USD

 

የኩነቱ ዓይነት

በመደበኛ ጊዜ  

የዘገየ

ጊዜው ያለፈበት  

እርማት

 

ቅጂ

 

ማረጋገጫ

1 ልደት 30 40 50 40 50 20
2 ጋብቻ 30 40 50 40 50 20
3 ፍቺ 30 40 50 40 50 20
4 ሞት 20 30 40 30 50 20
5 ጉዲፈቻ 30 40 50 40 50 20

 

ማሳሰቢያ፡-

  • መደበኛ የምዝገባ ጊዜ ልደት በ90 ቀን ሲሆን የተቀረው ኩነት በሙሉ በ30 ቀን ውስጥ መመዝገብ አለበት
  • በመደበኛው የምዝገባ ወቅት ሳይመዘገብ ቀርቶ እስከ አንድ ዓመት ባለው የዘገየ ሲሆን
  • ከአንድ ዓመት በኋላ የሚደረግ ምዝገባ ጊዜው ያለፈበት ይሆናል፡፡

 

 

        

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook